Objective Of Engineering and Construction Ethiopia

ድርጅቱ አላማዎች የሚከተሉት ናቸው፤
1. በኢንጂነሪንና ኮንስትራክሽን ተያያዥነት ያለው ኢኮኖሚያዊ፣ ሰብዓዊ እና ማህብራዊ ተሳትፎን ማሳደግ
2. ኢንጂነሪንና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ማሣደግና ማጎልበት፤ ትምህርትና የምርምር ሥራዎች እንዲበረታቱ ማድረግ፤ የውይይትና ንቅናቄ መድረኮችን ማዘጋጀት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ማከናወን ፣መጽሔቶችንና ጽሑፎችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት፤
3. በኢንጂነሪንና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ የሚገኙትን የዲዛይን፤ የማቴሪያልና የኮንስትራክሽን ሕጎች፤ ስታንዳርዶችና ኮዶች በሚሻሻሉበት፤ በሚዳብሩበትና በሚዘጋጁበት ጊዜ የሚፈለገውን አስተዋጽኦ ሁሉ ማድረግ፤
4. በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንጂነሪንና ኮንስትራክሽን ተዛማጅ የሙያ መካከል ሊኖር የሚገባውን ሙያዊ ዝምድናና ግንኙነት ማጎልበትና ማሳደግ፤
5. በኢንጂነሪንና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች እና ሞያተኞች የሙያ እና ሰብዓዊ መብቶች ማስጠበቅና ማዳበር፤ ድህነትና ጤና ማስጠበቅ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ማከናወን፣ ብሎም የሙያውን ክብር ከፍ ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት ማድረግ፤
6. በኢንጂነሪንና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሴቶችን ተሳትፎ እንዲጨምር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ማከናወን ሙያ እና ሰብዓዊ መብቶች ማስጠበቅና ማዳበር፤
7. በኢንጂነሪንና ኮንስትራክሽን ዘርፍ የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ላይ ግንዛቤ ማዳበር፤
8. የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ ማዳበር፤
9. በኢንጂነሪንና ኮንስትራክሽን ዘርፍ የላቀ አስተዋጽዖ ላደረጉ ዕውቅና መስጠት፤
10. ሌሎች በኢንጂነሪንና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተግባራት ማከናወን፤

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *